የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት እና ዴሞክራሲ

May be an image of monument

የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት ዴሞክራሲነት!

======================================

ጹሑፉ የገዳ ሥርዓት ምንነት የሚለውን ፅንሰ _ሃሳብ (concept) እና በገዳ እና ሥርዓቱ ላይ የተለያዩ የታርክ ፀሐፊዎች (Antiyopology) ያሉትን እናያለን። በመቀጠል የገዳ ዴሞክራሲነት ከነባራዊ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር እንዴት እንደሚገለፅ በጥቅቱ አይተን ምሁራኖች በሰጡት አስተያየት ተነስተን ዘመናዊ ዴሞክራሲ እና የገዳ ሥርዓት ተመሣሣይነት እና ልዩነት ምን እንደሆነ እናያለን፣ ቀጥሎም የገዳ ሥርዓት በፓርላመንታዊ እና ፕሬዚዳንታዊ ዴሞክራሲ ውስጥ ምን ዓይነት ድርሻ እንዳለው አይተን ጹሑፉን እቋጫለሁ።

ምዕራፍ 1

ገዳ

ገደ ማለት ምን ማለት ነው? ይህንን ጥያቄ ለመመለስ Amin የተባለ አንድ ፀሐፊ መሐመድ ሐሰን የተባለ የቦረና ኦሮሞ ዋቢ በመጥቀስ እንዴፃፈው “ገዳ ማለት ከለላ ወይም ጥላ በመባል ከሚታወቅ ቃል የመጣ ነው “በማለት ይገልፃል ።

ፀሐፊው እንደገለፀው ይህ ከለላ ወይም ጥላ በሚባለው ቃል ሦስት ትርጉም በውስጡ ያካትታል። እነሱም 1ኛ መጠለያ (Shelter )፣ 2ኛ መሸሸጊያ (for taking refuge )፣ 3ኛ ጥላ ወይም በኦሮሞ ቋንቋ Guddisa የሚባለው (Umbrella )እንደማለት ነው።” ይላል።

ከዚህ ትርጉም ውስጥ ከለላ ወይም ጥላ የሚለው ቃል ኦሮሞ የሚወደው እና የሚያከብረው በሥሩ ስለማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮቹን የሚወያይበት “ኦዳ” የሚባለው ታርካዊ እና ትልቁ ዛፍ ጋር ለማነፃፀር ተፈልጐ ነው።

ያም ሆነ ይህ ገዳ እና ከለላ ወይም ጥላ ለማነፃፀር የተሞከረው ጽንሰ ሃሳብ የሚናቅ አይደለም። በሌላ በኩል ግን አንዳንድ የአስትሮፖሎጂ ፀሐፊዎች ማለትም እንደ አስመሮም ለገሠ እና ባክስታር የመሳሰሉት ” ገዳ ማለት ዘመን ፣ ዕድሜ እና ዓመት “እንደሆነ ይገልፃሉ ።ኦሮሞ ስንት ዓመት ነው በማለት ዕድሜ ይጠያየቃል ፣ ዘመንን ደግሞ ስንት ገዳ ነው በማለት ይጠያየቃል ። ስለዚህ ከላይ ፀሐፊዎች የሰጡት አስተያየት እና የህዝቡን ስንመለከተው “ገዳ ማለት ዕድሜ እና ዘመን መሆኑን እንረዳለን።

ምዕራፍ 2

የገደ ሥርዓት (The Gada System)

የገደ ሥርዓት ምንነት ላይ ፀሐፊዎች የተለያየ አመለካከት አላቸው ።ከፊሎቹ “ገዳ ኦሮሞ ስለ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮቹን የሚመራበት ከባህሉ የመነጨ ሥርዓት ነው ” በማለት ይገልፃሉ ።እንደ ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሠ ያሉ ጸሐፊዎች ደግሞ ” ገዳ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሥርዓት ብቻም ሳይሆን ኦሮሞ ኢኮኖሚውን የሚመራበት ሥርዓትም ጭምር ነው “ይላሉ።

የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት ዴሞክራሲነት በምን ይገለፃል?

ፕሎዎድን የተባለ አንድ የታርክ ፀሐፊ የገዳ ሥርዓት ማንነት ስገልፅ “Among the Republican system, Gada is superior “ትርጉሙም “ከማንኛውም ሪፑብልካዊያን በበለጠ ገዳ የበላይ ነው ።”ማለቱ ነው። ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሠም ይህንን ሃሣብ ስያጠናክሩ “Gada System is one of the most astonishing and instructive turns the evolution of human society has taken “ትርጉሙም “የገዳ ሥርዓት በሰው ልጅ ዕድገት (evolution )ውስጥ አስደናቂ የሆነ ብዙ ታላላቅ ለውጦች የታየበት ሥርዓት ነው “በማለት ይገልፃል።

ባክስታር የተባለ ፀሐፊ “ኦሮሞ አስደናቂ የገዳ ሥርዓት ቢኖረውም ዕድሜያዊ መዋቅር (age sets) የሆነ አስተዳደራዊ ሥልጣን የሌለው፣ በፖለቲካዊ ጉዳዮች በቀጥታ የማይገናኝ፣ በአስተዳደራዊ ጉዳይ ውስጥ ምንም ዓይነት ድርሻ እንደሌለው እና ግጭትን መፍታት እንደማይችል ይናገራል ።ይሁን እንጂ ብዙ ፀሐፊዎች ከባክስታ ሃሳብ ጋር አይስማሙም ።ምክንያቱም በገዳ ሥርዓት ውስጥ የሚገኙ የዱባሌ፣ ታናናሽ ጋሜ፣ ታላላቅ ጋሜ ፣ ኩሳ እና ራባ ገዳ የተባሉ ደረጃዎች ሳያልፍ ወደ አባገዳ ሥልጣን የሚመጣ አንድም የኦሮሞ ልጅ አይኖርም ።እነዚህ የገዳ ሥርዓት እርከኖች ለሥልጣን የሚታጩ ሰዎች ልምድ እንድያገኙ እና የገዳ ሥርዓት ሃላፊነት መሸከም እንድችሉ እና ራሳቸውን የሚያዘጋጁበት አድካም (rite of passage )ያለው እና በዓለምአቀፍ የተደነቀ ሥርዓት ነው። ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሠ ይህንን እንዲህ በማለት ይገልፃሉ ” it is a system of classic (sets of );that succeed each other every eight years in assuming Military ,political & Economic ritual responsibilities of the Gada System is an institutional that represention extreme development of a type of social structure known ; anthropologist as age sets “ይላሉ። ትርጉሙም ” ገዳ የዕድሜ መዋቅር ሆኖ በእየ ስምንት ዓመት የሚቀባበሉት ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ዓላማ ያለው ተቋም ያቀፈ ነው። እንዴ አንትዮሮፖሎጂስቶች አገላለጽ በዕድሜ ላይ የተመሰረተ ትልቅ ዕድገት እና ከፍተኛ ሕዝባዊ መዋቅር የሚታይበት ሥርዓት ነው “ይላሉ። እንዴ ፀሐፊው አባባል የኦሮሞ ፀጋ እና እምነት የሆነው ዋቄፈና በዚህ ሥርዓት ይመራል። በተጨማሪም የኦሮሞ ፍልስፍና ግኝት እና ሕግ የሆነው የጊዜ መቁጠሪያ “ካላንደርም”ምንጩ ገዳ ሥርዓት እንደሆነ ይታሰባል ።ባኪስታሪ የተባለ ፀሐፊም”የገዳ ሥርዓት በቃል የሚገልፅ በተግባርም የሚታይ ፖለቲካዊ ፍልስፍና ነው ።” ይላል ።በአጭሩ የገዳ ሥርዓት ከኦሮሞ ባህል ውስጥ የመነጨ ሕግ ሆኖ ኦሮሞ እርስ በእርሱ የሚተዳደርበት እና የሚተዳደርበት ፣ መብቱን እና ግደታውን የሚለይበት፣ አገሩን ፣ ኢኮኖሚውን እና እምነቱን የሚፈፅምበት ሃሣቡን የሚገልፅበት ፣ ፍላጎቱን የሚያሟላበት ሥርዓት ነው።

ይሁን እንጂ ገዳ የኦሮሞ ብቻ ነው ?የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም ።እዚ ላይ መታወቅ ያለበት አንድ ነገር በደቡብ ኢትዮጵያ የሚኖሩ ኩሽ ሕዝቦች ማለትም ሲዳማ ፣ ጌድኦ ፣ ወላይታ ፣ አዲያ ፣ ኮንሶ …ወዘተ ልክ እንደ ኦሮሞ ገዳ የሰው ልጅ መሠረታዊ ኑሮ የሚያቅፍ ባይሆንም የራሳቸው የሆነ ገዳ ሥርዓት አላቸው ።እንዲሁም በሱዳን የኑዌር ሕዝብ በኬንያ ማሳዮታ እና ኩኩዩ ገዳ አላቸው።

ይሁን እንጂ የገዳ ሥርዓት ምንጩ ከኦሮሞ ነው ወይስ ከኩሽ ነው ?የሚለው ጥያቄ ለምርምር ክፍት እናድርገው ።አንድ እውነታ ግን የገዳ ሥርዓት ኦሮሞ ዘንድ ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በስፋት እና በጥልቀት ስመራበት እና ስሰራበት የኖሬ ሥርዓት ነው።

የገዳ ሥርዓት እንዴት እና መቼ ተጀመረ ?የሚል ጥያቄ ልነሳ ይችላል ። የገዳ ሥርዓት መቼ እንደተጀመረ ከመቼ ጀምሮ ሥራ እንደዋለ ትክክል የሆኖ የተቀመጠ መረጃ ባይኖርም እንደኦሮሞ ታርክ መረጃ መሠረት ከ500 ዓመት በፊት ስሰራበት እንደነበረ ይገመታል ። ፕሮዊት የተባለ ፀሐፊ ሐሬሮ ከማታ የሚባል ታርክ አዋቂ የቦረና ኦሮሞ ዋቢ በመጥቀስ ከ4000 ዓመት ጀምሮ ኦሮሞ የገዳ ሥርዓት ስተዳደርበት እንደነበረ ገልፀዋል።

ምህራፍ ሦስት

የገዳ ሥርዓት በምን ይገለፃል ?

አንድ ፕላዎድን የተባለ ፀሐፊ የገዳ ሥርዓት ማንነት ስገልፅ “Among the Republican system ,gada is superior ” ከማንኛውም ሪፑብልካዊያን በበለጠ ገዳ የበላይ ነው ።ማለቱ ነው ።አስመሮም ለገሠም ይህንን ሃሳብ በማጠናከር “Gada System is one of the most astonishing & instructive turns the evolution of human society has taken “ትርጉሙም “የገዳ ሥርዓት በሰው ልጅ ዕድገት (evolution )ውስጥ አስደናቂ የሆነ ብዙ ታላላቅ ለውጦች የታየበት ሥርዓት ነው “በማለት ይገልፃል ።ባክስታር የተባለ ፀሐፊ “ኦሮሞ አስደናቂ የገዳ ሥርዓት ቢኖረውም ዕድሜያዊ መዋቅር (age sets) የሆነ አስተዳደራዊ ሥልጣን የሌለው ፣ በፖለቲካዊ ጉዳዮች በቀጥታ የማይገናኝ ፣ በአስተዳደራዊ ጉዳይ ውስጥ ምንም ዓይነት ድርሻ እንደሌለው እና ግጭትን መፍታት እንደማይችል ይናገራል ።ይሁን እንጂ ብዙ ፀሐፊዎች ከባክስታ ሃሳብ ጋር አይስማሙም ።ምክንያቱም በገዳ ሥርዓት ውስጥ የሚገኙ የዱባሌ፣ ታናናሽ ጋሜ ፣ ታላላቅ ጋሜ ፣ ኩሳ እና ራባ ገዳ የተባሉ ደረጃዎች ሳያልፍ ወደ አባገዳ ሥልጣን የሚመጣ አንድም የኦሮሞ ልጅ አይኖርም ።እነዚህ የገዳ ሥርዓት እርከኖች ለሥልጣን የሚታጩ ሰዎች ልምድ እንድያገኙ እና የገዳ ሥርዓት ሃላፊነት መሸከም እንድችሉ እና ራሳቸውን የሚያዘጋጁበት አድካም (rite of passage )ያለው እና በዓለምአቀፍ የተደነቀ ሥርዓት ነው ። ስለዚህ የገዳ ሥርዓት የዕድሜ እና አስተዳደራዊ ቅንጅት የለውም የምል ሃሳብ ተቀባይነት የለውም ።

በአጭሩ በዚህ በገዳ ሥርዓት ውስጥ የሚታወቁ ታላላቅ ጉዳዮች የሥርዓቱ ዓላማ ከሪፑብልካዊያን ጋር መመሳሰሉ ነው

ምህራፍ አራት

የገዳ ሥርዓት እና የዴሞክራሲ ተመሳሳይነት እና ልዩነት ።

ከላይ የገዳ ሥልጡንነት መዳሰስእንደሞከርኩት ከአስትሮኖሚ አመለካከት በመነጨ የራሱ ካላንደር ፣ የራሱ የሆነ አስተዳደር የማህበራዊ አስተሳሰር እነደሆነ ይታወቃል ።ይሁን እንጂ ከአንዳንድ ሁኔታ የተነሳ የገዳ ሥርዓት ዴሞክራሲ(classic democracy)ከዓለም ዴሞክራሲ ሥልጣኔ ጋር እንዳይራመድ እና ወደ አድሱ የዴሞክራሲ ግኝት እራሱን ማሳደግ (transcend)ማድረግ አልቻለም ።በተለያየ ጊዜ ብቅ ስሉ የነበሩት ገዥ መደቦች ሊያቀጭጩት እና ልያጠፉት ሞክሮ ነበር። ስለዚህ እንደ ምህራብያዊያኖች ሥልጣኔ (western civilization) ከሌሎች ዓለም ሥልጣነ የሚጠቅመውን በመውሰድ ራሱን አሻሽሎ እና አዳብሮ ከወቅቱ ሁኔታ ጋር መራመድ አልቻለም። ሌሎች የዓለም ሃይማኖቶች ማለትም ክርስቲያን እና እስላም በቅደመተከተል በመግባት የምህራባዊያን ዴሞክራሲ(western democracy) እና የምስራቅያዊያን ዴሞክራሲ(Oriental democracy)መሰረት የሆነውን የራሳቸውን እምነት ለማስፋፋት ስባል ስፈፅሙበት የነበረው ድርጊት ለገዳ ሥርዓት ዕድገት ምቹ ሁኔታ አልፈጥረለትም። በዚህ እና በመሳሰሉት ምክንያቶች የገዳ ሥርዓት ከዘመኑ ዴሞክራሲ ጋር ልዩነት እና ተመሳሳይነት ልኖረው ችሎአል።

የገዳ ሥርዓት እና የዘመኑ ዴሞክራሲ ልዩነት

የገዳ ሥርዓት ዴሞክራሲነት በሁለት ጎራ ተቀናጅተው በአካል እና በአህምሮ ዳብሮ (socialization process)አልፎ በሥልጣን ላይ ሃላፊነት መውሰድ መቻል አለበት።ይህ በምህራብዊያን ዴሞክራሲ ዘንድ ደካማ ነው።

በገዳ ሥርዓት ዴሞክራሲ classical ውስጥ ሥልጣን ለመያዝ ስባል ማመፅ እና የመገዳደል ባህል የለም ።እንዲሁም የአማባግሸን ባህልም የለም። የፖለቲካ ሹመት እና ሥልጣን (authority) በእንስትውትሽናል (Institutional) በሆነ መንገድ ብቻ ነው ሥልጣን ከአንዱ ወደ አንዱ የሚተላለፈው ።ሥልጣን ከአንዱ ወደ አንዱ በሚተላለፍበት ወቅት ሥልጣን የሚያስተላልፈውም ሆነ ሥልጣን የሚቀበለው አባሎቻቸውን ከብት አርደው አብልቶ አጠጥተው ጨፍሮ አስጨፍሮ ቡታ ድግስ የሚባለውን ሥርዓት ላይ የፖለቲካ ሥልጣን የሚረካከቡት።

የኦሮሞ ገዳ ዴሞክራሲ በዕድሜ ሁኔታ ማህበራዊ አደረጃጀት ያለው ሲሆን በዚህ አደረጃጀት ላይ ተንተርሶ መብት እና ግዴታ ይሰጣል ።

የዘመናዊው ዴሞክራሲ ግን እንደዚህ ዓይነት አደረጃጀት የለውም ።

የገዳ አባል በመሆን የፖለቲካ ፣ የወታደራዊ እና የዋቀፌታ እምነት ሃላፊነት መውሰድ የሚችል ወንድ ብቻ ነው ።ይህ ጉድለቱ ሲሆን በምህራብዊያን ዴሞክራሲ ዘንድ ግን በሁሉም ሃላፊነት ወንድ እና ሴት እኩል ናቸው።

በምዕራብያዊያን ዴሞክራሲ የለሌው በኦሮሞ ገዳ ሥርዓት ውስጥ የአባቶች ገዳ እና የልጆች ፓርቲ ገዳ በመባል በሁለት ተለይተው አለ ። ሁለቱም የራሱ የሆነ አምስት አምስት ፓርቲ አለው ።ለምሳሌ በቦረና ኦሮሞ ውስጥ የገዳ ሥልጣን ቢርመጅ ፣ መልባ ፣ ሙዳ፣ ሮበሌ ዱሎ የሚባሉ የአባቶች ገዳ ፓርቲ ስኖሩ እንዲሁም በልጆች ገዳ ፓርቲ ውስጥ ደግሞ አልዳዳ ፣ ኦራታ፣ ብፎሌ ፣ ሱቡቃ እና ክሎሌ የተባሉትን ፓርቲዎች አሉአቸው ።ሁለት ዙር (two sami cycles)40 ዓመት በፊት የአባቶች ገዳ ስሆን የቀረው 40 ዓመት ደግሞ የልጆች ገዳ ፓርቲ ይሆናል ። በምህራብዊያን ዴሞክራሲ ውስጥ ሃይማኖትና መንግሥት (in principal) የተለያዩ ናቸው ።በገዳ ሥርዓት ግን ገዳ እና ቃሉ ይተጋገዛሉ።

የገዳ ሥርዓት እና የዘመኑ ዴሞክራሲ ተመሳሳይነት

ልክ እንደ ምህራብያዊያኖች ዴሞክራሲ የገዳ ሥርዓትም አስተዳዳሪዎቹን ለተወሰነ ጊዜ ይመርጣቸዋል ህዝቡ ነው የሚመርጣቸው የመመረጥ ብቃትም ወሳኝ ነው ።እንደአስፈላጊነቱ የህዝቡን መብት የማያስከብር ከሆነም የተመረጠውን ከሥልጣን የሚያወርደውም ሕዝቡ ነው ጠባቂም ይሾማል ።

የገዳ ሥርዓት ልክ እንደ ምህራብያዊያኖች ዴሞክራሲ አስተዳደራዊ መዋቅሩ እስከ ቀበሌ ድረስ አለው ።በቀበሌም በእየጎሳ ጠቅላላ ስብሰና(ጉባኤ)አለው ።ማንኛውም ሰው በተለያየ ጉባኤ ላይ ተሳትፎ ሃሳቡን በነፃነት ይገልፃል ።የፈለገውን ደግፎ የፈለገውን ለመቃወም ሙሉ መብት አለው ።በዚህ ረገድ ገዳ ሥርዓት እና የምህራባዊያን ዴሞክራሲ በጣም ይመሳሰላል ።

ሁለቱም ዴሞክራሲ የሕዝባቸውን መብት እና ግዴታ የሚደነግግ ሕግ አላቸው ።የገዳ ሥርዓት ህግ ልክ እንደ ምህራብያዊያኖች ዴሞክራሲ ሕግ የተፈጥሮ እንክብካቤ ሕግ አለው።የነፍስ ጥበቃም ሕይወት ላሌውም ለሌለውም (animate & inanimate object )የመሳሰሉት አሉት ።የሁለቱ ዴሞክራሲ መመሳሰል በዚህ አጭር ጹሑፍ መግለፅ ይከብዳል ።

ምህራፍ 5

የገዳ ሥርዓት በዘመኑ ዴሞክራሲ ውስጥ ልኖረው የሚችለው ሚናገዳ በአፍሪካ ቀንድ አከባቢ ለተለያየ ሁኔታ እና ዓላማ በጥቅም ላይ ሲውል እንደነበረ በትንሹም ቢሆን ለመጠቃቀስ ሞክረነዋል ።በኢትዮጵያ ውስጥም ኦሮሞ ፣ ሲዳማ ፣ ወላይታ ፣ ኮንሶ፣ አዲያ ፣ ጌድኦ እና ወዘተ በኬንያ ውስጥ በእንደ መሳይ እና ኩኩዩ በሱዳን የኑዌር ሕዝብ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ ።

ይህንን የገዳ ሥርዓት እንደአስፈላጊነቱ በማጠናከር እና ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ተሻሽሎ እንዲሰራበት ቢደረግ ለምስራቅ አፍርካ ህዝቦች ሠላም እና አብሮ መኖር ውስጥ የጎላ ሚና እንዳለው ይታመንበታል ።በአገር ውስጥም ለህዝቦች ሠላም እና መቀራረብ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል ።ሥራ ወዳድ ዜጋ ፣የተነሳሽነት ፍላጎት ኖሮት ሠርቶ ራሱን ለማስተዳድር የሚችል በመፍጠር ረገድ በተለየ በኦሮሞ ገዳ ሥርዓት ውስጥ ማላመድ (socialization process) በእየደረጃ የሚሄድ እንድጠናከር ማድረግ ትልቅ ውጤት አለው።በገዳ ሥርዓት ውስጥ ያለውን የመደማመጥ ባህል እና ሃሳቡን በነፃነት የመግለፅ መብት በቀጣይነት እንዲጠናከር በማድረግ ዴሞክራቲክ እና ዴሞክራሲን ለማሳደግ (ለማዳበር)ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ።

ለትግበራውም ትልቅ እና ጥልቀት ያለው ምርምር ማካሄድ ይጠበቃል ።የገዳ አባቶች የባህል መሪዎች ተከታታይነት ያለው ግኑኙነት መፍጠር አስፈላጊ ነው ።በተለያየ ጊዜ እና ቦታ የሚደረግ አገርአቀፍ እና ዓለምአቀፍ ጉባኤዎች ላይ የገዳ አባቶችን በማሳተፍ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የገዳ ሥርዓት ሕጎችን ተሻሽሎ እንዲሠራ ማድረግ አስፈላጊ ነው ።ለምሳሌ የቦረና ገዳ ብንመለከት በእየስምንት ዓመቱ የሚደረግ “ጉሚ ጋዮ”(Gumii Gaayyoo)የሚጠራ ጉባኤ አለ ።የዚህ “ጉሚ ጋዮ”ዓላማም ከጊዜ ወደ ጊዜ ከወቅቱ ሁኔታ ጋ ሊዛመድ የማይችል ሕጎችን ለመሻር እና ጊዜው የሚጠይቅ አድስ ሕጎች ለመጨመር ታስቦ ነው ።

የገዳ ሥርዓት ጉባኤዎች በሃሳብ ፣ በገንዘብ ፣ በዕውቀት እና በማቴሪያል በማጠናከር መብት እና ግዴታ የሚደነግግ የባህል ህግ ወሰን ለማስከበር እርስ በእርሱ የገዳ ሥርዓት ሕጎችን (ዴሞክራሲን የሚያስታርቅ)ገምግመው ለመሻርም ሆነ ለማሻሻል እንዲችሉ ማገዝ አስፈላጊ ነው ።

Harbar Liws የተባለ ተመራማሪ እንዲህ በማለት ይገልፃል “In this connection utilizing or making creative use of gada System than trying to weaken or destroy it & it …could play a vital role in the correct political life it nurture & permitted to flourished “”የገዳ ሥርዓት ለማጥፋት ወይም ለማስቀረት ከመልፋት ይልቅ ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ ሁኔታ በማዘጋጀት ባለው የፖለቲካ ሁኔታ ውስጥ እንድያብብ ፣ እንድጠናከር ማድረግ በጣም አስፈላጊ እና ለነገ የማይባል ጉዳይ ነው ።”ይላል።

(የጌታቸው ቡልቲ ቅኝት)